Friday, December 20, 2013

8 ቁጥሯ



 አቤት ልስላሴ አቤት ደም ግባቷ

 ጠይሙ ገላዋ ልዩ ነው ውበቷ

 ትከሻዋ ጠባብ ዳሌዋ ሞንዳላ

ወገቧ ቅጥነቱ እፍኝም አይሞላ

አይቻት አላውቅም ለቤቱ እንግዳ ናት

ከጠረዼዛው ላይ ያውም እርቃኗን ናት

ሳልተዋወቃት ሳይኖረን ሠላምታ

 ሂጄ ጉብ አልኩባት አይቻት ላንድ አፍታ

 እጄን ወዲያው ልኬ ወደ ትከሻዋ

ዳበስ እያደረኩ ብደርስ ከወገቧ

 ቅጥነቱን ወደድኩት አጥብቄ ያዝካትኝ

ዓይን ዓይኗን እያየው ወደኔ ሳብካትኝ

የወይራ መዓዛ ጠረኗ ማረከኝ

 በሥሜት ተውጬ ከንፈሯን ሳምኩትኝ

 ወደላይ ሥገፋት ረካ ሥሜቴ

 ልቤ ረሰረሰ ተቆርጦ ጥማቴ

 ቆራሱማ ውሃ ነበር የያዘችው

8 ቁጥሯ ቅል ጥሜን ያረካችው
                 
 yitesam z - harar