ኢትዮጵያዊነት ፣ ብሔር እና ሰው መሆን
ብዙ ግዜ ብሔርተኝነትንም ይሁን ኢትዮጵያዊነትን የሚያቀነቅኑ ግለሰቦች አንድን ነገር ሲዘነጉ ይስተዋላል፡ በዚህም የተነሳ አብዛኛውን ማህበረሰብ ግራ ያጋቡታል።
ነገር ግን ሁሉም ሊያስታውሰው እና ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ነጥብ ሰው መሆንን ነው።
እንደኔ እምነት ሁለቱም ወገኖች የራሳቸው እውነት አላቸው
በየራሳቸው መንገድ ትክክልም ናቸው ስለዚህ ሁለት ትክክል የሆኑ ነገሮችን እንደ ተቃራኒና ተፃራሪ ነገር ከማየት ይልቅ የሚታረቁበትን መንገድ መገንዘብ ተገቢ ነው ይህም ሰው መሆን ነው ማንም ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊነትን ከፍ ያረገ መስሎት ብሔሮችን ካላከበረ ፣ብሔሮች ራሳቸውን ከፍ ያረጉ መስሏቸው የሌላውን ብሔር ግለሰብ ካዋረዱ ሁሉም ከንቱ ነው። እውነታው ይህ ነውና አንድ ሰው ሌላውን ሰው ሰው በመሆኑ ብቻ ቢወደው ሙሉ ማንነቱን መቀበል አይከብደውም ብሔሩን ፣ ቋንቋውና ባሕሉን ያከብርለታል ፡አንዱ ያንዱን ብሔር ፣ ቋንቋና ባሕል ካከበረ በአድነቱ ማሰሪያ በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ ማሕበረሰብ ይፈጠራል።
ያኔ ኢትዮጵያዊነት ፍቅር ነው ብለን በሙሉ ልብ ቀና እንላለን
ቅደም ተከተሉም ይህ ነው
ሰው
ብሔር
ኢትዮጵያ
No comments:
Post a Comment