እንቆቅልሽ
አንድ ሰው ተራበ
እጆቹን ታጠበ
መዓድ አቀረበ
የገበታው ዓይነት መዓዛው ቢያውድም
ለተራበ ስጋው ያቀረበው ሁሉ ምን በቂ ቢሆንም
ዕትኡ በሰላም እስኪባል አልበላም
እንቆቅልሽ
ሌላውም ተርቦ
እጆቹን ተጣጥቦ
ማዕዱን አቅርቦ
ካማረ ገበታው ካረደው ፍሪዳ ከጠላ ከጠጁ
ሊጠጣ ሊበላ ቢዘረጋም እጁ
ፍላጎት ግን ከዳው
በድኑን አስቀምጦ መንፈሱ ግዜ አጣ ሐሳብ
አነጎድው
እንቆቅልሽ
አንድም ከዚ አለ
ተርቦ የዋለ
ምን ርሃብ ቢሰማው ቢጨማደድ ፊቱ
ምን ቢጮህም ወስፋቱ
እጁን አይታጠብ
ማዕዱን አያቀርብ
ጥግ ይዞ ተቀምጧል
በደከሙ ዓይኖቹ ህዝቡን ያማትራል
እንቆቅልሽ
አማኝ ነብሱን ብሎ
ሐብታሙ ሲጨነቅ
ድሃው ግን በማጣት
ሶስት ሰወች ተራቡ ዓለም እንደዚ ናት
እንቆቅልሽ ህይወት እንቆቅልሽ ዓለም
ከጥያቄ በቀር ምን ጊዜም መልስ የለም!!!!!!!
No comments:
Post a Comment